የአዳማ ከተማ ም/ቤት ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤ በአዳማ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት ጅባ የተመራ የም/ቤቱ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ መድረክ ያካሄደ ሲሆን በልምድ ልውውጡ መድረክም የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እና የም/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የአቅመ ደካሞች ቤት ምርቃት እና የርክክብ ስነ-ሥርዓት ተካሄደ፤ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች የተገነቡ 9 የአቅመ ደካሞች ቤቶች የምርቃት እና ቤቶቹን ለባለቤቶቹ የማስረከብ ስነስረአት የተካሄደ ሲሆን በስነስረአቱ ላይም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አመራሮች የኮሪደር ልማት አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄዱ፤ የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እቅድ እና አፈፃፀም በኘሮጀክቱ ጽ/ቤት አመራሮች የቀረበ ሲሆን አሁን የደረሰበት ደረጃ በዝርዝር በምክር ቤቱ አመራሮች ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
የድሬደዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈትሂያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በአርባምንጭ ከተማ በተዘጋጀው የ19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ሲምፖዚየም ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ።
የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
"ህብረብሄራዊነታችን ለብዝኀነት እውቅና የምንሰጥበት አንድነታችንን የምናጠናክርበት ቀን ነዉ" ሲሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ተናገሩ።
"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለማክበር በተዘጋጀው መሪ እቅድ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና የበአሉ አብይ ኮሚቴዎች ውይይት አካሂደዋል::
የጳጉሜ 4 የህብር ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን "ኅብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን እለቱን አስመልክቶ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውኗል።
የድሬደዋ አስተዳር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የጳጉሜ ቀናት የእንኳን አደረሳቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
ዛሬ ማለዳ ድሬዳዋ የገባው ልኡካን ቡድን የተለያዩ መርሀ ግብሮችን ያከናወነ ሲሆን በመጀመሪያም በሀይስኩል ጋራ በመገኘት ከድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ጋር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሂደዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የምክክር ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን በይፋ ለኮሚሽኑ አስረከቡ፤
የአምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ ተካሄደ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ዘርፍ አካላትን ያካተተው ልኡካን ቡድን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከክልሉ ም/ቤት የፍርድ ቤቶች የዳኝነት ለውጥ ፍኖተ ካርታ እና የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አተገባበር ላይ እና ሌሎች ምርጥ ተሞክሮዎች ላይ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ በትላንትናው እለት ሀዋሳ የገቡ ሲሆን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እና ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ከማኔጅመንት አባሎቻቸው ጋር እንዲሁም የምክር ቤቱ ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘነበ ዘርፉን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት እንግዶቹን በሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት እንኳን ደህና መጣችሁ 'ዳኤ ቡሹ' ብለው ተቀብለዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ ዘርፍ አካላትና የአስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ የ3 ወራት እቅድ ላይ በጋራ ውይይት ተካሄደ፤
ድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎች የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ፡፡
የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላትን የያዘ ልዑክ በአስተዳደሩ የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ጉብኝት አካሄደ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና የምክር ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የሆኑት የድሬዳዋ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፣ የድሬዳዋ ብዙሀን መገናኛ ድርጅት እና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ሰራተኞች 19ኛውን የጸረ ሙስና ቀንን አስመልክቶ የፓናል ውይይት ተካሄደ