የክረምት በጎ አድራጎት የቤት እድሳት መርሃ-ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት ጋር የእቅድ ውል ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ፤
የአዳማ ከተማ ም/ቤት ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤ በአዳማ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት ጅባ የተመራ የም/ቤቱ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ መድረክ ያካሄደ ሲሆን በልምድ ልውውጡ መድረክም የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እና የም/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
የአቅመ ደካሞች ቤት ምርቃት እና የርክክብ ስነ-ሥርዓት ተካሄደ፤ በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች የተገነቡ 9 የአቅመ ደካሞች ቤቶች የምርቃት እና ቤቶቹን ለባለቤቶቹ የማስረከብ ስነስረአት የተካሄደ ሲሆን በስነስረአቱ ላይም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አመራሮች የኮሪደር ልማት አፈፃፀም ላይ ውይይት አካሄዱ፤ የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እቅድ እና አፈፃፀም በኘሮጀክቱ ጽ/ቤት አመራሮች የቀረበ ሲሆን አሁን የደረሰበት ደረጃ በዝርዝር በምክር ቤቱ አመራሮች ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል።
የድሬደዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈትሂያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር እና የድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በአርባምንጭ ከተማ በተዘጋጀው የ19ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ሲምፖዚየም ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ።
የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
"ህብረብሄራዊነታችን ለብዝኀነት እውቅና የምንሰጥበት አንድነታችንን የምናጠናክርበት ቀን ነዉ" ሲሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ተናገሩ።
"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለማክበር በተዘጋጀው መሪ እቅድ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና የበአሉ አብይ ኮሚቴዎች ውይይት አካሂደዋል::
የጳጉሜ 4 የህብር ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን "ኅብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን እለቱን አስመልክቶ የተለያዩ ፕሮግራሞች ተከናውኗል።