• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

ምክር ቤቱ በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አንቀፅ ፲፪ የተደነገገው መሰረት
ሀ. ህግ ያወጣል፣

ለ. የአስተዳደሩን በጀት ያጸዴቃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል ይቆጣጠራል፣

ሐ. አስተዳደራዊ አካላትን ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘውም እርምጃ ይወስዳል፣

መ. በምክር ቤቱ የተለያዩ ኮሚቴዎችንና ሌሎች አስፈሊጊ አካላትን ያቋቁማል ያደራጃል፤

ሠ. በምክር ቤቱ የሚሰየሙ፣ የሚመረጡ እና የሚሾሙ የአስተዳደሩን የመንግስት ባለስሌጣናት ይሰይማል፤ ይሾማል፤ ይመርጣል።

ረ. የምክር ቤቱ አባላት ከመረጣቸው ህዝብ ጋር እንዱገናኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል።

ሰ. የተቋማትንም ሆነ የህብረተሰቡን ጥቆማና አቤቱታዎች ያስተናግዳል።

ሸ. ሌሎች የምክር ቤቱ ስልጣን የሆኑ ተግባራትን ያከናውናል።

የአስተዳደሩን ረቂቅ በጀት በአስተዳደሩ ካቢኔ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ከቀረበ

  • የበጀት አመቱ ከመጀመሩ ከአንድ ወር በፊት ረቂቅ በጀቱ በጥቅል እና በዝርዝር ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ መቅረብ አለበት፣
  • በረቂቅ በጀቱ ላይ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃሊፊ መግልጫ መስጠት አለበት፣
  • ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መግላጫ በመቀጠል ምክር ቤቱ በመርህ እና በአጠቃላይ በጀቱ ላይ ውይይት ማካሄዴ አለበት፣
  • በመጨረሻም በጀቱ ለምክርቤቱ አባል ቀርቦ በጉባኤ ይጸድቃል

አገልግልቱን ለማግኘት የሚጠየቅ ቅድመ ሁኔታ

  • ተቋማት መንግስት በሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት ከረጅም ዓመት የልማት እቅድ የመነጨ የበጀት አመቱን እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ አለበት
  • ተቋማት በቁጥጥር እና ክትትል ወቅት ቋሚ ኮሚቴው የሰጠውን ግብረ-መሌስ በእቅድ ውስጥ አካቶ ማቅረብ አለበት፣
  • በምክር ቤቱ ለተቋሙ በካፒታል ፕሮጀክት ያፀደቃቸው ስራዎች እና በጀቶች ዕቅድ ውስጥ መካተት አለበት፣
  • በህዝብ ውክልና በህብረተሰብ ተቋሙን የሚመለከት የተነሱ ችግሮች ለመፍታት በእቅድ ውስጥ መካከት አለበት፣
  • ተቋማት እቅድ ግምገማው ከመካሄዱ አንድ ወር በፊት የተቋሙ ኃሊፊ የፈረመበት ሰነድ በሀርድ እና በሶፍት ማቅረብ አለበት፣

ከተገልጋይ የሚቀርቡ ቅሬታና ጥቆማዎች ተቀብሎና አግባብነቱን መርምሮና አጣርቶ ተገቢውን ምሊሽ መስጠት

አገልግልቱ የሚሰጥበት ቦታ፡- በቋሚ ኮሚቴዎች

አገልግልቱን ለማግኘት የሚጠየቅ ቅዴመ ሁኔታ

  1. ምክር ቤቱ በሚከተለት ጉዳዮች ላይ ጥቆማዎችን እና አቤቱታ ይቀበላል፡-
    • በአስተዳደሩ ወይም በህዝብ ሀብት እና ጥቅም ላይ የደረሰ ወይም ሉደርስ የሚችል ጉዲትን በሚመለከት፣
    • ህገ-መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከተፈጠረ ወይም ይፈጠራል ተብሎ ሲገመት፣
    • የመንግስት ፖሉሲ እና ስትራቴጂ የሚያደናቅፍ ሁኔታ ሲከሰት፣
    • በህዝቦች መካከል ግጭት ከተፈጠረ ወይም ግጭት ሊያስነሳ የሚችል ሁኔታ ሲያጋጥም፣
    • የሰብዓዊ መብት ሲጣስ፣
    • ከፍተኛ የሆነ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት፡፡
  2. ጥቆማው ወይም አቤቱታው በጽሁፍ ተዘጋጅቶ የጠቋሚውን ስም፣ ሙለ አዴራሻ እና ፊርማ የያዘ መሆን አለበት፣
  3. ማንነቱን የሚገሌፅ መታወቂያ መያዝ ይጠበቅበታል፣
  4. ምክር ቤቱ ወይም ኮሚቴዎቹ የጠቋሚዎችን ማንነት በሚስጢር መያዝ አለበት፣

 

  • በዓመት 2 ጊዜ እና ምክር ቤቱ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ጉዳይ አባላቱ ከህዝብ ጋር ተገናኝተውና ሀሳብ አሰባስበው እንዱያቀርቡለት ፕሮግራም ያዘጋጃል
  • ምክር ቤቱ አባላት ያዘጋጁትን ሪፖርት ይቀበላል፣ እንደአስፈሊጊነቱም መፍትሄ ይሰጣል እንዱሁም ለምክር ቤቱ ተግባራት በግብዓትነት ይጠቀምበታል፡፡ የተላለፈ ውሳኔ ሲኖርም አፈፃፀሙን ይከታተላል፣
  • በየምርጫ ጣቢያው አባሉ ለምክር ቤቱ ሪፖርት አባላት ማቅረብ አለባቸው

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!