የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አከባበር አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
ክብርት አፈ ጉባኤዋ በመግለጫቸውም መላው የአስተዳደሩን ነዋሪዎች ለ19ኛ ጊዜ ለሚከበረው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል '' ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት '' በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች እንደሚከበር ገልጸው የበአሉ የማጠቃለያ ስነስረአትም በአርባ ምንጭ ከተማ እንደሚካሄድ ገልጸዋል። በመሆኑም እንደ ድሬዳዋ አስተዳደርም የፌዴራሊዝም ጽንሰ ሀሳብን እና የህገመንግስታዊ አስተምህሮን ባማከለ መልኩ በተለያዪ ኩነቶች እንደሚከበር ገልጸዋል። በአሉ ሲከበርም አንድነታችንን እና ህብረብሄራዊነታችንን የምናጠናክርበት እንዲሁም የኢትዮጵያን ከፍታ የምናረጋግጥበት በአል እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል። በመሆኑም ሁላችንም ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የነበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት በህገመንግስቱ ምላሽ ያገኘበት ህገ መንግስቱ የጸደቀበት ቀን ስለሆነ እንዲሁም የዘንድሮው በአል የብልጽግና ፓርቲ የ5ኛ አመት ምስረታ በሚከበርበት ወቅት መከበሩ ልዩ ትርጉም እንዲኖረው ያደርገዋል ብለዋል ። የበአሉም አካል የሆኑ የሴቶች፣ የወጣቶች እና የሲቪል ሰርቫንት መድረኮች እንደሚካሄዱ እና እንደአስተዳደር የማጠቃለያ ኘሮግራም በህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም በደመቀ ሁኔታ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።
ይህን ዜና አጋራ