• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

የህጻናት ፓርላማ ጠቅላላ ጉባኤ 

ሕጻናት በሚመለከታቸው ጉዳዮች ላይ የመሳተፍ መብታቸውን ለማረጋገጥና ድምጻቸው እንዲሰማ ለማስቻል የተለያዩ ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን በተለይም ሕጻናት በተደራጀ ሁኔታ ድምጻቸውን ለማሰማት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ይህንን ጥረት ለመደገፍ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት በከተማ ሞዴል የህጻናት ፓርላማዎችን በማቋቋም እና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት፣ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ፣ በገንዘብበ ቁሳቁስና እንዲሁም የተለያዩ ሙያዊ ድጋፎችን በማድረግ  በቀበሌዎች የህጻናት ፓርላማዎች እንዲቋቋሙ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪ  በ2004 ዓ.ም እንደ አገር አቀፍ ደረጃ  የተዘጋጀውን  የህጻናት ፓርላማ መመሪያ በአስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ በመቀየር  ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል፡፡  

ይህ የህጻናት ፓርላማ መመሪያ እስካሁን ድረስ የሕጻናት ፓርላዎችን ለማቋቋም፣ ለማጠናከርና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉም መመሪያ ሆኖ በማገልገል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን አሁን በተደረሰበት የግንዛቤ ደረጃና በስራ ሂደት የታዩ ውስን  ክፍተቶችን ለማረም ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት እንዲሻሻል የተደረገውን በመቀበል ወደ አስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ ቀይሮ ለመጠቀም እንደሚከታለው አዘጋቷል፡፡    

መመሪያው በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን ክፍል አንድ ጠቅላላ ድንጋጌ፣ ክፍል ሁለት የህጻናት ፓርላማ አመሰራረትና አደረጃጀት፣ ክፍል ሶስት የህጻናት ፓርላማ የስብሰባ ስርዓትና የአባላት ሥነ-ምግባር፣ ክፍል አራት የህጻናት ፓርላማ ተመራጮችና የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ተግባራትና ኃላፊነት፣ ክፍል አምስት የባለድርሻ አካላት ሚና እና ልዩ ልዩ ደንጋጌዎችን ይዟል ፡፡    

የመመሪያው ዓላማ                                        

የመመሪያው ዋና ዓላማ በየደረጃው የሕጻናት ፓርላማዎች የሚቋቋሙበትን ሥርዓት ግልጽ በማድረግ፣ ከተቋቋሙ በኋላም ተግባራዊ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጉዳዮችንና ሊከተሏቸው የሚገቡ መርሆዎችና የአሠራር ሥርዓቶች በማሳየት እንዲሁም የህጻናት ፓርላማዎችን የማቋቋም፣ የማስተዳደር፣ የመደገፍና የማጠናከር ሚናና ኃላፊነት ያለባቸው አካላት ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት እንዲከተሉና ሚናና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማስቻል መብትና ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚያስችል የህጻናት ፓርላማዎች ማቋቋም፣ ማጠናከርና ትርጉም ያለው የህጻናት ተሳትፎ እንዲኖር ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው

የህጻናት ፓርላማ ጠቅላላ ጉባኤ 

   ሀ. አፈ ጉባኤ

   ለ. ም/አፈ ጉባኤ

   ሐ. ጸሃፊ

   መ. 6 ቋሚ ኮሚቴዎች

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!