• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት ጋር የእቅድ ውል ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ፤

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ከአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት ጋር የእቅድ ውል ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት አካሄዱ፤

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች እና የአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት የ2018 በጀት አመት የእቅድ ውል ስምምነት የፊርማ ሥነ-ስርዓት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ፣ ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ፣ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

 

 በፊርማ ስነ ስረአቱ ላይም ንግግር ያደረጉት የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በ2017 በጀት አመት እንደ ድሬዳዋ አስተዳደር በህግ አውጪ በህግ አስፈጻሚ እና በህግ ተርጓሚ በተለያዩ ማእቀፎች አመርቂ ውጤቶች መመዝገቡን አስታውሰው በ2018ም ከባለፈው አመት በተለይም በአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ከኑሮ ውድነት ፣ ከፕሮጀክቶች እና ከህዝብ ጥያቄ  አንጻር እንዲሁም ድሬዳዋ ከጀመረችው የስማርት ሲቲ ስራዎች በ2018 የሚገባደድበት እና በአስተዳደር ደረጃም ለህዝብ የተገባው ቃል እንደመጨረሻ አመት የሚገመገምበት እና ለህዝቡም ሌላ ቃል የሚገባበት አመት ስለሆነ አስፈጻሚው አካልም ሆነ ህግ አውጪው አካል ጊዜ የለኝም በሚል መንፈስ የተዘጋጀውን እቅድ የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ በሚሰጣቸው ግብረ መልሶች እና በህዝብ ውክልና የህዝብ ጥያቄዎች ታክለውበት እና ተገምግሞ ለፊርማ ስነስረአት መዘጋጀቱን ገልጸው ለእቅዱ መሳካት ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ርብርብ ሊደረግበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

 

በመቀጠልም የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች ከአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላት አመራሮች ጋር የፊርማ ሥነ-ስርዓቱን አካሂደዋል።

 

ዜና ፦ አዲሱ ካሳ 

ፎቶ ፦ እንድሪያስ ደሱ

 

#መረጃ  | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️ 

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 

 

ድህረ-ገጽ [Website]

www.ddacouncil.gov.et 

 

ፌስቡክ [Facebook]

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d 

 

ዩቲዩብ [YouTube]

https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP 

 

ቲክ ቶክ [Tik Tok]

https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1 

 

ቴሌግራም [Telegram]

ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!