• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ መልዕክት
የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ

የዲሞክራሲ ሥርዓት ለመገንባት፣ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና መልካም አስተዳደርን ለማስፈንም ሆነየዜጎችን መብት ለማስከበርና የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከሚያስችሉ ተቋማት መካከል ዋናዎቹ በየደረጃው የተቋቋሙ ምክር ቤቶች ናቸው::  የአስተዳደራችን ምክር ቤትም ከተቋቋመበት ጊዜ እንስቶ እስካሁን ድረስ ባከናወናቸው ህግ የማጽደቅ፣ ውክልናን የመወጣት፣ የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት ያስመዘገባቸው ውጤቶችም አበራታች ናቸው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ በትኩረት ከሚሰራቸው የፖለቲካና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች መካከል ዋናው የመራጩን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን መከታተል ነው፡፡

በአገር አቀፍም ሆነ በአስተዳደራችን የሚካሄዱ የፖለቲካና የመንግስት ሥራዎች ሳይደበላለቁና አንዱ ሌላውን ሳይተካ በተቀመጠላቸው አግባብ የሚከናወኑት በም/ቤቶች በፀደቁ የህግ ማዕቀፎች አማካኝነት ነው፡፡ የልማትሥራዎቻችንም/ቤቶች ባፀደቋቸው የህግ ማዕቀፎች የማይሰሩ ቢሆን ኖሮ የሚከናወኑ ማናቸውም ተግባራት የመራጩን ህዝብ ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች ከመመለስ ይልቅ የተወሳሰቡ ሁኔታዎች እንዲከሰቱና ህብረተሰቡም በምርጫ የሰጠንን ሃላፊነት እንዳንወጣ የሚያደርጉ ቀውሶች ይፈጠሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት የም/ቤቶች ሃላፊነትና አስፈላጊነት እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ለመጠቆም ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ምክርቤታችንም ሆነ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት መገንዘብ ያለባቸው መሰረታዊ ጉዳይ በ2013 ዓ/ም በተካሄደው 6ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ህብረተሰቡ ለብልጽግና ፓርቲ የሰጠው ይሁንታ ነው፡፡

የአገራችን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በምርጫው ያደረጉት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ኢትዮጵያን አሸናፊ ያደረገ ብቻ አልነበረም፡፡ የተካሄደው ምርጫ ከቀደሙ አምስት ምርጫዎች የተለየ ብቻ ሣይሆን ዜጎች መልዕክቶቻቸውንና ፍላጎቶቻቸውን የተንፀባረቀበት ነበር፡፡ ምክንያቱም ፓርቲያችን በከፍተኛ የህዝብ ድምጽ የተመረጠው ባከናወናቸው ተግባራትና ባስመዘገበው ውጤቶች እንዲሁም በገባው ቃል መሰረት መሆኑመታወቅ ይኖርበታል፡፡ ይህን በድልና በዕድል የተገኘን ውጤት የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፊነት ያለብንም እና በተግባር ለመፈፀም ከምክር ቤት አባላት ጀምሮ በተለያዩ የአመራርነት ደረጃ ላይ የምንገኙ አካላት መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል፡፡አስፈፃሚው አካል የሚሰጠው አገልግሎት መራጩን ማህበረሰብ የሚያረካ አገልግሎት መስጠት የሚቻለውም ምክር ቤታችን ያፀደቃቸውን የህግ ማዕቀፎች ሳይሸራረፉ በመተግበርና ቋሚ ኮሚቴዎች በሚከናውኗቸው የክትትልና ቁጥጥር ተግባራት ነው፡፡ በየዘርፉ ለሚከናወኑ ተግባራት ውጤታማነትም ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለብልጽግና ፓርቲ ይሁንታቸውን የሰጡት የፓርቲያችን መነሻ፣ ማኮብኮቢያና መዳረሻ ብልጽግና መሆኑን ስለተገነዘቡም መሆኑን ከግምት በማስገባትየብልጽግና ጉዟችንን የሚያሳኩ ተግባራትን ማከናወንም ከምንም በፊት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡

ተቋማችን በዋናነት ከሚሰራቸው የፖለቲካ ሥራዎች ጎን ለጎን የምክር ቤታችንን አገልግሎት የሚያጠናክሩና የመራጩ ህዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱና ህዝቡ የሰጠንን ሃላፊነት እንድንወጣ ነው፡፡ የምክር ቤታችንን ተልዕኮና አላማ የሚያሳኩ አሰራሮችን ለመዘርጋትና ለመተግበር፣ የመራጩንህዝብ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ለሚያላቅቁና ለብልጽግና ጉዟችን ስኬታማነት አስተዋጽኦ ለሚያበረክቱ ተግባራት ውጤታማነት የድሬዳዋን ነዋሪዎች የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ህዝባችን የሰጠንን ሃላፊነት በተግባር ለመፈፀም በጋራ እንቀሳቀስ በማለት መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡

መደመር መንገዳችን ብልፅግና መዳረሻችን ነው!

አመሰግናለው !

የተከበሩ አቶ ሻኪር አህመድ
ረዳት የመንግሥት ተጠሪ

የተከበሩ አቶ ደረጀ ፀጋዬ
ረዳት የመንግሥት ተጠሪ

የተከበሩ አቶ ገዛኸኝ ታዲዎስ
ረዳት የመንግሥት ተጠሪ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!