የአቅመ ደካሞች ቤት ምርቃት እና የርክክብ ስነ-ሥርዓት ተካሄደ፤
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራዎች የተገነቡ 9 የአቅመ ደካሞች ቤቶች የምርቃት እና ቤቶቹን ለባለቤቶቹ የማስረከብ ስነስረአት የተካሄደ ሲሆን በስነስረአቱ ላይም የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የጽ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ፡፡
ፕሮግራሙን አስመልክቶም ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ አመርቂ ውጤት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸው የብልጽግና ፓርቲም ከሁሉም በላይ ክቡር የሆነውን ሰው ልጅ ክብር በመስጠት የዜጎችን ክብር ለማረገገጥ የሚያስችሉ ስራዎች በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል። በተለይም ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ኢኒሼቲቭ ተጀመሩ በጎ ስራዎች በመላው አገሪቱ በመሰራት ላይ እንደመሆናቸው በድሬዳዋ አስተዳደርም በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በተለያዩ ቦታዎች የ9 አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት በመስራት እና አስፈላጊ ግብአቶችን በማሟላት በዛሬው እለት ለርክክብ በመድረሱ የተሰማቸውን ልባዊ ደስታ በመግለጽ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ምክር ቤቱ ባለው ውስን በጀት ለድሬዳዋ አስተዳደር ስለሚያደርገው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል፡፡
በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ ስለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን ገልጸው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዜጎች ህይወት የተሻለ እንዲሆን ህጎችን በማውጣት እና የወጡ ህጎች ምን ያህል ተግባራዊ እየተደረጉ ነው የሚለውን በመከታተል እና በመቆጣጠር የተሻሉ ስራዎች እንዲሰሩ በየደረጃው ካሉ የመንግስት መዋቅሮች እና ህዝብ ጋር የሚሰራ ተቋም ነው ብለዋል። በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረትም የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ድሬዳዋን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በመጨረሻም የቤቶቹ ባለቤቶች ከተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ እጅ የመኖሪያ ቤቶቹን ቁልፍ ተረክበዋል።
ዜና፦ አዲሱ ካሳ
ፎቶ ፦ እንድሪያስ ደሱ
#መረጃ | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!
ድህረ-ገጽ [Website]
www.ddacouncil.gov.et
ፌስቡክ [Facebook]
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d
ዩቲዩብ [YouTube]
https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP
ቲክ ቶክ [Tik Tok]
https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1
ቴሌግራም [Telegram]
ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤
ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን!
ይህን ዜና አጋራ