• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

"ህብረብሄራዊነታችን ለብዝኀነት እውቅና የምንሰጥበት አንድነታችንን የምናጠናክርበት ቀን ነዉ" ሲሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ተናገሩ።

"ህብረብሄራዊነታችን ለብዝኀነት እውቅና የምንሰጥበት አንድነታችንን የምናጠናክርበት ቀን ነዉ" ሲሉ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባኤ ተናገሩ።

 

ሀገራዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ከክልል አፈጉባኤዎች እና ከሚዲያ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ 

 

19ኛዉ የኢትዮጵያ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት "በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የፓናል ዉይይት ተደርጓል። 

 

በውይይቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ኀላፊዎች ፣ የክልልና የሁለቱም ከተማ መስተዳድር አፈጉባኤዎች እና የሚዲያ ሃላፊዎች እንዲሁም ጋዜጠኞች ተገኝተዋል። 

 

የፌዴሬሽን ምክር ቤት  አፈጉባዔ የተከበሩ አቶ  አገኘሁ ተሻገር የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንዲከበር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሲወስን ለዘላቂ ሰላምና ለዴሞክራሲ ግንባታ ያለዉን ድርሻ ከግምት በማስገባት ነው ብለዋል።

 

በዓሉ ኢትዮጵያውያን ባሕልና ወጋቸዉን የሚያስተዋዉቁበት እና ለሀገር ገጽታ ግንባታ የተለያዩ ሥራዎች የሚከናወኑበት ነዉ ሲሉም ገልጸዋል። 

 

በተለያዩ ጊዜያት የተካሄዱት በአሎች ላይ በአስተናጋጅ ክልሎች ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎች በስፋት የታየበት እና የህዝብን አንድነት የሚያስተሳስር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር መቻሉን የታየበት መሆኑን ጠቁመዋል ።

 

የህብር አንድነትን በጋራ በማስተሳሰር ህብረብሔራዊ አንድነት ለህዝባችን የምናበረክተው እሴት ነው ያሉት አፈጉባኤው የጋራ መስተጋብር የሆነውን የጋራ ትብብራችንን በኢትዮጵያ ያሉ የብዙሃን መገናኛ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝበው በከፍተኛ ኃላፊነት ሊሰሩ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

 

አቶ አገኘው ተሻገር የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች መብት መከበር ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና የተረጋገጠበት ቀን ነዉ ብለዋል። 19ኛው የኢትዮጵያ ብሄርብሔረሰቦች ቀን ከህዳር 25 ቀን ጀምሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉንና ሀገራዊ  አንድነትን የሚያጠናክር እና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትም የሚያረጋግጥ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል። 

 

ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በሀገር ግንባታ ላይ ያላቸዉ ድርሻ በአግባቡ ባለመሰነዱ ችግሮች ሲፈጠሩ ቆይተዋል፤ እነዚህን የተሳሳቱ ትርክቶች ማረም ደግሞ የሁሉም ኀላፊነት መሆኑን አመላክተዋል። 

 

ዕለቱን በማስመልከት የፓናል ዉይይት ተካሂዷል። በውይይቱ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ያግዛሉ የተባሉ ሀሳቦች ተነስተዋል።

 

ምንጭ :- Diretv አማርኛ ህዳር 2/2017

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!