የአዳማ ከተማ ም/ቤት ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤
በአዳማ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት ጅባ የተመራ የም/ቤቱ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት በመገኘት የልምድ ልውውጥ መድረክ ያካሄደ ሲሆን በልምድ ልውውጡ መድረክም የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እና የም/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በመድረኩም የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት በአደረጃጀት በይበልጥ ከጨፌ ኦሮሚያ ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ገልጸው ም/ቤቱ የተለያዩ የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን የምክር ቤቱን ሀላፊነት በሚገባ ለመወጣት የሚያስችሉ ስራዎች መሠራታቸውን በመግለጽ ይህን መሰል የልምድ ልውውጥ መድረኮች የሁለቱንም ም/ቤቶች አቅም ለማጎልበት እድል የሚፈጥር በመሆኑ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
በመቀጠልም የተከበሩ ወ/ሮ እመቤት ጅባ ባደረጉት ንግግርም በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋናቸውን በመግለጽ ለልምድ ልውውጡ ድሬዳዋን ተመራጭ እንድትሆን ያደረጋት በተለይም በመልካም አስተዳደር ፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በትራፊክ ደህንነት እና ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶች ምክንያት ጥሩ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም የሚያስችል መሆኑ በመታመኑ ነው ብለዋል በመሆኑም ም/ቤቱን ለማዘመን እና ከወረቀት ነጻ ለማድረግ የተሰራው ስራ በልዩ ተሞክሮ የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸዋል።
በመቀጠልም የልምድ ልውውጥ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በምክር ቤቱ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችንም ተዟዙረው ተመልክተዋል።
በመጨረሻም የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን አና በአስተዳደሩ የተሰሩትን የኮሪደር ልማት ስራዎችን እንዲሁም የድሬደዋ አስተዳደርትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ባለስልጣንን ጎብኝተዋል፡፡
ዜና አዲሱ ካሳ
ምስል ሐየሎም
ይህን ዜና አጋራ