• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

ራዕይ

በ2ዐ18 ሴት የምክር ቤት አባላት አቅማቸው ጐልብቶ የውሣኔ ሰጪነት ደረጃ እኩል ተጣቃሚና ተሳታፊ ሆነው ማየት፡፡

ተልእኮ

የሴት የም/ቤት አባላት መብት እና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ አቅማቸውን በመገንባት፣ የተጣለባቸውን የውክልና ተግባር በአግባቡ እንዲወጡ እና ተሳትፎአቸውን ከፍ እንዲል ሁኔታዎችን በማመቻቸት፣ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚነታቸውን በማረጋገጥ በልማቱ ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን ሚናቸውን እንዲወጡ ማስቻል ነው ፡፡
እሴቶች

  • የህግ የበላይነትን ማክበር፣
  • አሣታፊና ፍትሀዊ የሆነ አሰራር መከተል፣
  • የጾታ እኩልነትን ለማስፈን በቁርጠኝነት መስራት፣
  • የሴቶች ተሳታፊነት እነ ተጠቃሚነት ማሳደግ፣

የኮከስ ተግባርና ኃላፊነት

  • የተለያዩ ኮሚቴዎችን በመቋቋምና የተለያዩ ዘዴዎችን    በመጠቀምፖሊሲነክ    ወቅታዊ መረጃዎችን …ወዘተ ለአባላት በማድረስ    የአባላትን ብቃትና    በራስ    የመተማመን ሁኔታ የማጎልበት፣ ለሴት ተመራጮች በተለያዩ ጊዜያት የውይይት መድረክ በማዘጋጀት    አቅማቸውን    ማጎልበት፣
  • ሴት የምክር ቤቱ አባላት ህግ ሊወጣላቸው ስለሚገቡ የሴቶች    ጉዳዮች ላይ ሀሳብ    ዘገባ እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
  • በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ መሰል ተቋማት ማህበራትና ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የልምድ ልውውጥ ማድረግ የሴቶችን    የምርጫ ተሳትፎ ለማጎልበት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ማከናወን፣
  • በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች ከመከላከል ከሚመለከታቸው ጋር ተቀናጅቶ የበኩሉን    መወጣት፣

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!