• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የ19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀንን አከባበር  አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሄደ፤

የ19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀንን አከባበር  አስመልክቶ የውይይት መድረክ ተካሄደ

 

"ሃገራዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦችን ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ለማክበር በተዘጋጀው መሪ እቅድ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና የበአሉ አብይ ኮሚቴዎች  ውይይት አካሂደዋል::

 

በመድረኩም በአሉን በአስተዳደር ደረጃ በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር በተዘጋጀው መሪ እቅድ ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በአሉ ማህበረሰቡ ባህሉን እና እሴቱን እንዲያስተዋውቅ ፣ በአስተዳደሩ ነዋሪዎች ዘንድ ጠንካራ መስተጋብር በሚያስጠብቅ መልኩ ለማካሄድ አንዲሁም ሃገራዊ ብሎም አስተዳደራዊ ገፅታን ከመገንባት አንፃር እንዲሁም ካለፉት አመታት የተገኙትን  ተሞክሮዎችን በማስፋት ዘንድሮም በተሻለ መልኩ ህገ መንግስታዊ ፌደራሊዝም አስተምሮት እንዲሁም ህብረብሄራዊነትን የሚያጠናክሩ የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች እንዲደራጁ አብይ ኮሚቴው ውይይት አካሂደዋል ::

አክለውም የተቋቋመው  አብይ ኮሚቴ እንደ አስተዳደር የብሔር ብሔረሰቦችን ቀን ለማክበር የተዘጋጀው መሪ እቅድ አመርቂ መሆኑን ገልፀው በተጨማሪም ህብረ ብሔራዊ አንድነት የሚገልፅና የአስተዳደሩን በጀት ባገናዘበ መልኩ ሁሉን አካታች እንዲሆን ሃሳብ ሰንዝረዋል::

በመጨረሻም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ፈቲህያ አደን 19ኛው ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በብዝሃነት እና አንድነት ገዢ ትርክትን ባሰፈነ መልኩ አንዲከበር አስተዳደሩ ያለበትን ቁመና ቃኝቶ የተለያዩ ዝግጅቶች እያከናወነ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ተተኪውን ትውልድ ስለ እሴቱና አንድነት የተገነዘበ ትውልድ በመፍጠር ሀገር ለማስረከብ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ስራዎችን ከመተግበር አንፃር ዘርፈ ብዙ የትኩረት አቅጣጫዎች መቀመጣቸውን ገልፀዋል::

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!