• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የጳጉሜ 4 የህብር ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፤

የጳጉሜ 4 የህብር ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፤

 

በድሬዳዋ አስተዳደር ጳጉሜ 4 የህብር ቀን "ኅብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን እለቱን አስመልክቶ የተለያዩ ፕሮግራሞች  ተከናውኗል።

በመጀመሪያም ጠዋት 12 በምድር ባቡር አደባባይ ከተለያዩ የማህበረብ ክፍሎች ከተውጣጡ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የማስ ስፖርት ፕሮግራም  የተካሄደ ሲሆን በመቀጠልም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙበት መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ኢትዮጵያ የባለብዙ ብዝኃነት የረጅም ታሪክ ባለቤት ሀገር ስትሆን  በነዚህ ለሀገር መሠረት በሆኑ የብዝሃነት መገለጫዎች ማለትም በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በባህል፣ በፖለቲካዊ አመለካከት፣ በመልክዓ ምድር አቀማመጥ እና  በአየር ጸባይ  ብዝኃነት ተቃኝታ የተሠራች  ሀገር መሆኗን ገልጸው  ይህን ብዝሃነት ግን በአግባቡ እውቅና ሰጥቶ መስተናገድ ባለመቻሉ ሀገራችን የምትፈልገው የእድገት ደረጃ እንዳትደርስ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት የለውጥ ዓመታት ለዘመናት የተዘሩ የጥላቻ ነጠላ ትርክቶችን  በወል ኅብረ-ብሔራዊ ትርክቶች ለማረም እና ልዮነትን በአግባቡ ማስተናገድ የምትችል ዲምክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን እናተስፋ ሰጪ ውጤትም እየታየ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በመቀጠልም ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር በድሬዳዋ አስተዳደር የተረጋጋ ዘላቂ  ሰላም እና ፀጥታን ለማረጋገጥ ህብረ ብሄራዊነትን የተላበሰ ተቋም እና የፖሊስ ሀይል በመደራጀቱ እና ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ሰላሟ በእጅጉ ተረጋግጧል፤ ይህም ድሬዳዋን ለኑሮ የበለጠ ምቹ እንድትሆን ከማድረጉ በላይ ለንግድና ኢንቨስትመንት ይበልጥ ተመራጭ እንድትሆን ተጨማሪ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።

በመድረኩም የ2017ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንየት በማድረግ ለመንግስት ሰራተኞች አነስተኛ የደሞዝ ተከፋዮች የተለያዩ ድጋፍ ስነ ስርዓት እና ሌሎች መርሃ ግብሮችም ተከናውነዋል።

4/13/2016

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!