የድሬደዋ አስተዳር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የጳጉሜ ቀናት የእንኳን አደረሳቹ መልእክት አስተላልፈዋል።
የተከበሩ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በመልእክታቸውም እያንዳንዱ ቀናት የተሰጠውን ስያሜዎች አላማ እንደሀገር የተጀመሩትን ለውጦች የሚጠናከሩበት ፤ ያገጠሙንን ፈተናዎች ደሞ አንደ ድልድይ ተሻግረን የምናልፍበት አመት አንዲሆን የነዚህ 5 የጳጉሜ ቀናትን ለህዝባችን ተደራሽ መረጃዎችን እየሰጠን እንዲሁም የጀመርናቸውን ጠንካራ ጎኖች እያበረታታን ያሉትን ችግሮች ደግሞ እያረምን እና እያስተካከልን ከህዝብ ጎን መሆናችንን የምናሳይበት ቀን ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ በ5ቱ የጳጉሜ ቀናት ስያሜ ዙሪያ እንደሚከተለው ማብራሪያ ሰጥተዋል ።
ጳጉሜ 1 የመሻገር ቀን
ይህ የመሻገር ቀን እንደ ሀገር የነበሩብንን እዳዎች የተሻገርንበት ቀን የሚታወስበት ቀን ነው እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ስኬቶች የሌማት ቱሩፋት ፣ የኮሪደር ልማት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ህዝበችን እንዲገነዘብ እያረግን ያሉትን ችግሮች ደግም በ2017 የሚፈታበት ቀን ነው
ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀን
እንደ ሀገር የጀመርናቸውን ሪፎርሞች የምናስቀጥልበት በተለይ የፍትህ አካላት ሪፎርም የሲቪል ሰርቫንት ሪፎርም እንደ ሀገር ደግሞ ትላልቅ ሪፎርሞቻችንን የምናስተዋውቅበት ከዛ ባለፈም አገልጋይነት እንደ ሀገር ፍቅር የምናሳይበት ቀን በእለቱ ቅዳሜ ቀንን ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለተገልጋዮች ክፍት በማድረግ የአገልጋይነት ስሜታችንን የምናዳብርበት ቀን ነው
ጳጉሜ 3 የሉአላዊነት ቀን
ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀኝ ግዛት ያልተገዛች ሀገር ናት በተለይ አባቶቻችን እቺን ሀገር በደም አስጠብቀዋል እኛ ደግሞ ጠብቀው የሰጡንን ሀገር በላብ እና በልማት የማበልጸግ አደራ እንዳለብን የምናስብበት እና የውጭ ግንኙነታችንን የምናጠናክርበት ቀን ይሆናል ብለዋል
ጳጉሜ 4 የህብር ቀን
ይህ ቀን እንደሀገርም ሆነ እንደ አስተዳደር ብዝሀነታችንን ለአንድነታችን ፣ ለልማትና ለስኬት የምንጠቀምበት ቀን በተለይ እንደ ድሬዳዋ የምንታወቅበት ወንድማማችነትና እህትማማችነት እሴታችንን አጉልተን የምናሳይበት ቀን
ጳጉሜ 5 የነገው ቀን
ይህ ቀን እንደሀገር እስካሁን ያሳካናቸውን ልማቶች የምናስቀጥልበት እና እንደሀገር የነበሩብንን እዳዎች ለትውልድ የምናስተላልፍበት ሳይሆን እዳዎቻችንን ጨርሰን ለቀጣዩ ትውልድ ተስፋን ብልጽግናን እና አንድነትን እንዲሁም ያደገች ኢትዮጵያን የምናስረክብበት ቀን ኢትዮጵያ እውነትም እንደ ሀገር የጀመረችውን እድገትና ብልጽግና ለማሳካት አቅሙም ብቃቱም ያላት መሆኑን የምናሳይበት ቀን ነው ብለዋል።
ይህን ዜና አጋራ