የድሬዳዋ አስተዳደር የፍትህ ዘርፍ አካላትና የአስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ የ3 ወራት እቅድ ላይ በጋራ ውይይት ተካሄደ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በመሩት የውይይት መድረክ ላይ የምክር ቤቱ እና የአስተዳደሩ የበላይ አመራሮች ፣ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሙያዎች የተገኙበት የውይይት መድረክ የተካሄደ ሲሆን የፍትህ ዘርፍ አካላትና የአስተዳደሩ ፍርድ ቤቶች የትራንስፎርሜሽን የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና የቀጣይ የ3 ወራት እቅድ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በመደምደሚያው የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት እና የበለጸገች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ የፍትህ አካላት በጋራ መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰባቸውን የቀጣይ የትኩረት ነጥቦችና አቅጣጫ እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ለማዘመን እና ለማህበረሰቡ ፈጣን ፍትህን ለመስጠት በፍርድ ቤቶች እየተሰሩ ያሉ የህግ ማእቀፎች በአጭር ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ፣ ከድሬዳዋም አልፎ ሀገር አቀፍ ደረጃ ጥሩ አፈጻጸም እያስመዘገበ ያለውን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን የሪፎርም ስራዎች መጠናቀቅ እንዳለባቸው፣ የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን የማጠናከር እና የፍትህ ተቋማት ችግር ፈቺ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በተለይም የአገልግሎት ፈላጊውን ህዝብ ጥያቄዎች መመለስ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፍ ፣ የአደረጃጀት እና የሰው ሃይል የማጥራት ስራዎች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ወደ አቅም ግንባታ ስራዎች መገባት እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም
ይህን ዜና አጋራ