• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

 የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላትን የያዘ ልዑክ በአስተዳደሩ የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ጉብኝት አካሄደ።

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላትን የያዘ ልዑክ በአስተዳደሩ የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ጉብኝት አካሄደ።

ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት እና የልምድ ልውውጥ በድሬዳዋ የሚገኙት የልዑካን ቡድኑ አባላት በትናንትናው ቆይታቸው የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን የለውጥ ስራዎች ተዘዋውረው መመልከት ችለዋል።

በዛሬው ጉብኝታቸው ከቃኟቸው ስፍራዎች መካከል የዓለም ዓቀፉን የእግር ኳሥ ማህበር ፊፋን የጥራት ደረጃ በማሟላት ማረጋገጫ ያገኘውን የድሬዳዋ አለም አቀፍ ስቴዲየም ፣ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ፣ የድሬዳዋን ወጣቶች የስፖርት አካዳሚ ፣ የጓሮ ሞዴል ችግኝ ጣቢያን ጨምሮ በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ የተሰየመው ፖርክ ይገኙበታል።

በጉብኝታቸውም ማብቂያ የድሬዳዋ እቻቸው ባከናወናቸው የለውጥ ስራዎች ዙሪያ የልምድ ልውውጥ መድረክ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የሶማሌ ክልል ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላቱን በሁለት ቀን ቆይታቸው የድሬዳዋን የልማት ትሩፋቶችን እና የተቋማትን ሪፎርሞች በመመልከታቸው አመስግነው ባለን ውስን በጀት የተከናወኑ ለውጦች ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

በመጨረሻም የልዑካን ቡድኑ አባላት በድሬዳዋ ቆይታቸው መደሰታቸውንና፣ ፍሬያማ ውይይት በማድረግ ተጨባጭ ተሞክሮ መቅሰማቸውን ተናግረዋል፤ ለአስተዳደሩ ምክር ቤትና ለአቻቸው በክልሉ መንግስትና ምክር ቤት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ለሁለት ቀናት በድሬዳዋ ከተማ ቆይታ ያደረጉት የልዑካን ቡድን ከአስተዳደሩ ልዩ ስጦታ ተበርክቶላቸው መርሃ ግብሩ ፍጻሜውን አግኝቷል።

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!