• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ዘርፍ አካላት ሪፎርም ልኡካን ቡድን በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ዘርፍ አካላት ሪፎርም ልኡካን ቡድን በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የልምድ ልውውጥ አካሄደ፤ 

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች እና የፍትህ ዘርፍ አካላትን ያካተተው ልኡካን ቡድን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከክልሉ ም/ቤት የፍርድ ቤቶች የዳኝነት ለውጥ ፍኖተ ካርታ እና የፍትህ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አተገባበር ላይ እና ሌሎች ምርጥ ተሞክሮዎች ላይ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ በትላንትናው እለት ሀዋሳ የገቡ ሲሆን የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ  መንግስት ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ እና ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ከማኔጅመንት አባሎቻቸው ጋር እንዲሁም የምክር ቤቱ ም/አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዘነበ ዘርፉን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በተገኙበት እንግዶቹን በሀዋሳ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት እንኳን ደህና መጣችሁ 'ዳኤ ቡሹ' ብለው ተቀብለዋል።

         

በዛሬው እለትም የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ደምሴ ዱላቻ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እና በክልሉ የተዋረድ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት  እና የፍትህ ዘርፍ አካላት ትራንስፎርሜሽን እቅድ በእስትሪንግ ኮሚቴ እየተመራ እስካሁን በለውጥ ፍኖተ ካርታው ያከናወኗቸውን ስራዎች፣  የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች እንዲሁም ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እና የፈቱበትን አግባብ በልምድ ልውውጥ መድረኩ ላይ ገለፃ አድርገዋል። 

 

የልዑካን ቡድኑ አባላት በሀዋሳ በነበረን ፍሬያማ ውይይት የቀሰሙትን ምርጥ ተሞክሮ በመቀመር ከአስተዳደሩ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ ተግባራዊ ለማድረግ እና የፍትህ ስርዓቱን በማሻሻል ረገድ የፍርድ ቤቶችን አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የበለጠ የህዝብ ተጠቃሚነትን እና አመኔታን ያተረፈ እንዲሆኑ ለማስቻል እንደሚሰራ የጋራ መድረክ ግንኙነት ለማጠናከር የልምድ ልውውጡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡ 

 

በመጨረሻም ለክልሉ ምክር ቤት፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እና ለሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በድሬዳዋ አስተዳደር  እና ምክር ቤት ስም ምስጋናቸውን አቅርበው ለሁለት ቀናት በሀዋሳ ከተማ ቆይታ ያደረጉት የልዑካን ቡድን አባላት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብሩ  ተጠናቋል። 

 

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ሀዋሳ፤

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!