• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የአምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ ተካሄደ።

የአምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ ተካሄደ።

 

በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የተዘጋጀ የምስራቅ ኢትዮጵያ አምስቱ ተጎራባች ክልሎች ማለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ፣ የሀረሪ ፣ አፋር ፣ ሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች የጋራ ምክክር መድረክ የክልሎችን የርስ በርስ የመንግስታት ግንኙነትን ሥርዓትን ለማጠናከር ታስቦ የአምስቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት  በድሬዳዋ ተካሂዷል።

 

የተጎራባች ክልሎች የጋራ የውይይት መድረክ መርሀ ግብርን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የመንግስታት ግንኙነት የዲሞክራሲያዊ አንድነትና ህገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ የተከበሩ ኢንጅነር ሙሃመድ ሻሌ የአምስቱ ምስራቅ ኢትዮጵያ ተጎራባች ክልሎች ፎረም ከዚህ ቀደም እንደ ሞዴል የሚጠቀስ  መሆኑን አስታውሰው አንዲህ ዓይነቱ የጎንዮሽ የመንግስታት ግንኙነት ተጎራባች ማህበረሠቦችን በመሠረተ ልማት በማስተሳሰር አንድነታቸውን ለማጎልበት አዎንታዊ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

በመድረኩም 2 ጥናታዊ የውይይት ጽሁፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በመጨረሻም 5 አባላትን የያዘ የ5ቱ አጎራባች ክልሎች ቴክኒካል ኮሚቴ በመምረጥ መድረኩ ተጠናቋል።

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!