ድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴዎች የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እና የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እንዲሁም ዳይሬክቶሬቶች ከፍተኛ ባለሞያዎች በተገኙበት የቋሚ ኮሚቴ የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ውይይት አደረጉ፡፡
የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እንዲሁም ዳይሬክቶሬቶች ከፍተኛ ባለሞያዎች በተገኙበት በተካሄደው የቋሚ ኮሚቴዎች የ9 ወር እቅድ አፈጻጸም የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን እና የምክር ቤቱ ፀሐፊ የተከበሩ አቶ ማርቆስ ባዩ መድረኩን መርተውታል፣ በመጨረሻም የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የ9 ወር የዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ በጠንካራ ጎን የታዩትን የምናስቀጥልበት በድክመት የታዩትን በቀሪ ወራቶች ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
ሚያዚያ/2016 ዓ.ም
ይህን ዜና አጋራ