• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

የሚጀመርበት ቀን

October 14, 2024

የሚጠናቀቅበት ቀን

October 14, 2024

አድራሻ

Dire Dawa Administration Council

ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ፤ የአብሮነታችን አርማ!

ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነታችን መገለጫ፤ የአብሮነታችን አርማ!

-------------------

ሰንደቅ ዓላማ የመስዋዕትነት፣ የነፃነትና የሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት አርማ ምልክት ነው፡፡ በእኛ ኢትዮጵያዊን ዘንድ ሰንደቅ ዓላማ ትልቅ ሥፍራና ትርጉም ያለው ነው፤ በልባችን የታተመ የአንድነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የነፃነታችንን መገለጫ ታላቅ ሀገራዊ  ዕሴት ፤ የአብሮነታችን ዓርማ ምልክት ነው፡፡

 

የሀገር ዳር ድንበርን ጥሶ ነፃነታችንንና ሉዓላዊነታችንን ለመውሰድ  በየዘመናቱ በተደጋጋሚ የመጣን የውጭ ወራሪ የጠላት ኃይልን እናት አባቶቻችን በተባበረ ክንድ በአንድት ቆመው መክተውና አሳፍረው የመለሱት ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ከሚሰጡት ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት በመነሳት ነው ፡፡ እንደዚሁም  ሰንደቅ ዓላማ ለሀገር  አንድነትና ሉዓላዊነት መፅናት አስተማማኝ ብሔራዊ መግባባት፤ ለአዲሱ ትውልድ ሀገራዊ ሪፎርምና ለውጥ ሙሉ ተስፋ እና ተጨባጭ መነሳሳት እንዲፈጠር ያስችላል። 

 

ስለሆነም ሰንደቅ ዓላማችን ተገቢውን ክብርና ገናና ከፍታውን ይዞ ከትውልድ ትውልድ ተላልፎ እነሆ ከአሁኑ ትውልድ ደርሷል፡፡ ለሰንደቅ ዓላማችንን  በማንኛውም ቦታና ጊዜ ተገቢውን ክብር መስጠትና ተገቢውን ክብር እንዲያገኝ ማድረግ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነትና ታሪካዊ  አደራም ጭምር ነው፡፡ 

 

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ አዋጅ ቁጥር ፰፻፷፫/፪ሺ፮ (እንደተሻሻለው) አንቀጽ ፪ መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል፡፡ 

 

የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል በያዝነው ዘንድሮ ዓመትም “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ ለ17ኛ ጊዜ በመላው ሀገሪቱ ለሚከበረው በዘንድሮ 2017 ዓ.ም  የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 4 ቀን በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች፣በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በየኢትዮጵያ ኢምባሲዎችና ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሰንደቅ ዓለማ በመስቀልና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም ሥነ-ስርዓት እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ የሚከበር ይሆናል፡፡

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት

ጥቅምት 2017 ዓ.ም

የሚከናወነወበት ቦታ ካርታ

https://maps.app.goo.gl/41m4uVc41bkAziSD8?g_st=com.google.maps.preview.copy

ይህን አጋራ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!