August 05, 2024
August 06, 2024
B- Capital Hotel, Dire Dawa, Ethiopia
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን በጋዜጣዊ መግለጫቸው መግቢያ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በራሳቸው እና በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም ክብርት አፈ ጉባኤዋ እንደጠቀሱት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሀምሌ 29 እስከ 30/2016 ዓ.ም ድረስ በ ቢካፒታል ሆቴል እንደሚያካሂድ ገልጸዋል፡፡
በጉባኤውም የድሬዳዋ አስተዳደር የ2016 በጀት አመት የአስፈጻሚ አካላት እና የማዘጋጃ ቤታዊ ሪፖርት እና የ2017 በጀት አመት እቅድ የሚቀርብ ሲሆን የምክር ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የ2016 በጀት አመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2017 በጀት አመት እቅድ እንደሚቀርብ እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶች እንደሚኖሩም ገልጸዋል፡፡
ይህን አጋራ