• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654

የሚጀመርበት ቀን

March 23, 2024

የሚጠናቀቅበት ቀን

March 23, 2024

አድራሻ

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 3ኛ አመት 7ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ የጀመረ ሲሆን የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የጉባኤውን አጀንዳዎች በማፀደቅ ጉባኤውን አስጀምረዋል።

አጀንዳዎቹም የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤ  ቃለ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፤ የድሬደዋ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2016 የ6 ወር  የስራ አፈፃፀም ሪፖርት፤ የድሬደዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች የዳኞች አስተዳደር ጉባኤን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ፤የድሬደዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤የድሬደዋ አስተዳደር የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤትን እንደገና ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ እና ሹመት እንደሚኖር ተገልጿል።

ሁለቱም ቃለ ጉባኤዎች ፀድቀው በአሁን ሰአት የድሬደዋ አስተዳደር የአስፈፃሚ አካላትና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2016  የ6 ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት የአስተዳደሩ ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከዲር ጁሀር በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
 

የሚከናወነወበት ቦታ ካርታ

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት

ይህን አጋራ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!