የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በዛሬው እለት የምክር ቤቱን 4ኛ የስራ ዘመን 1 አመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አስመልከቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የተከበሩ አፈ ጉባኤዋ በመግለጫቸው የምክር ቤቱ 4ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ጥቅምት 24/ 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልፀዋል።
በጉባኤውም የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁ ገልጸው የጉባኤው አጀንዳዎችም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ የስራዘመን የምስረታ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ ፣ የተለያዩ ደንቦችን ተወያይቶ ማፅደቅ፣ የተለያዩ ሹመቶችን የሚያፀድቅ ይሆናል።
በመሆኑም የተከበሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት በእለቱ በመገኘት በህዝብ የተጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ በምክር ቤቱ ስም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ዜና ናትናኤል ነጋሽ
ፎቶ፦ ሮቤል ወንደሰን
#መረጃ | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!
ድህረ-ገጽ [Website]
www.ddacouncil.gov.et
ፌስቡክ [Facebook]
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d
ዩቲዩብ [YouTube]
https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP
ቲክ ቶክ [Tik Tok]
https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1
ቴሌግራም [Telegram]
ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤
ይህን ዜና አጋራ