• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የ20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል የማጠቃለያ ኘሮግራም ተካሄደ

የ20ኛው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል የማጠቃለያ ኘሮግራም ተካሄደ

 

"ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት" በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አስተባባሩነት በአስተዳደር ደረጃ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ሲከበር የቆየው የ20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በአል የማጠቃለያ መርሀ ግብር በዛሬው እለት በእስፖርት አካዳሚ አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል።

 

በማጠቃለያ ኘሮግራሙ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር ፣ የአስተዳደሩ ም/ቤት አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ፣ ም/አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ፣ የመንግስት ዋና ተጠሪ የተከበሩ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ ም/ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ፣  የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ም/ቤት የቋሚ ኮሚቴ ተወካይ የተከበሩ ባንቺ ይርጋ ፣ የፌዴሬሽን ም/ቤት ፅ/ቤት ሀላፊ የተከበሩ አቶ ትግሉ መለስ ፣ የሀረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሱልጣን አብዱሰላም ፣ የሀረሪ ብሄረሰብ ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሂዲን መሀመድ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል። 

 

የበአሉን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ላለፉት 19 አመታት ሲከበር የቆየው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ብሄር ብሄረሰቦች የራሳቸውን ባህል ፣ ቋንቋ እና እሴት አንዲተዋወቁ እና እርስ በርስ ልምድ እንዲለዋወጡ እንዲሁም ህብረ ብሄራዊ አንድነታቸውን እንዲያጠናክሩ እድል መፍጠሩን ገልጸው በአገራችን የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ተግዳሮቶችን ለማስወገድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ዲሞክራሲ ፣ ፌዴራሊዝም እና የዜጋ ግንዛቤ ለማሳደግ ባለፉት አመታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል:: በህብረ ቀለማት የተዋበችና የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች መገኛ ትንሿ ኢትዮጵያ የሆነችው ድሬዳዋ ያላትን መልካም አሴቶች ለሀገር ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እና የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል። በመጨረሻም በበአሉ አከባበር ላይ የተሳተፉ ተቋማትን እና አመራሮችን በራሳቸው እና በም/ቤቱ ስም ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

 

በመቀጠልም የመድረኩንጨየመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተከበሩ አቶ ከድር ጁሀር የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የህዝቦች  የዘመናት የብዝሀነት የእኩልነት የፍትህና የዲሞክራሲ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኘበት ቀን እንደሆነ በመጥቀስ ብዝሀነትን ማስተናገድም ሆነ ሀገራዊ አንድነትን ከማረጋገጥ አንጻር የበአሉ መከበር ከፍ ያለ ፋይዳ አለው ብለዋል። 

አክለውም ህብረብሄራዊ የፌዴራሊዝም ስረአትን ማጠናከርን በተመለከተ ዜጎች ተገቢውን ግንዛቤ እንዲጨብጡ በማድረግ ብዝሀነትን በአግባቡ በማስተናገድ ህብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርአትን በማዳበር የበለጸገች ሀገርን እውን በማድረግ ረገድ የበኩላቸውን ሚና እንዲያበረክቱ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል በማለት በአሉን ስናከብር ሀገራዊና አስተዳደራዊ የልማት ኘሮጀክቶችን እና የተጀመሩ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ ስራዎችን ይበልጥ ለማጽናት ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

 

በበአሉ አከባበር ላይም የላቀ አስተዋጽኦ ያቀረከቱ ተቋማት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

 

በአዲሱ ካሳ

ፎቶ ፦እንድሪያስ ደሱ

 

#መረጃ  | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️ 

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 

 

ድህረ-ገጽ [Website]

www.ddacouncil.gov.et 

 

ፌስቡክ [Facebook]

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d 

 

ዩቲዩብ [YouTube]

https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP 

 

ቲክ ቶክ [Tik Tok]

https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1 

 

ቴሌግራም [Telegram]

ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤ 

 

ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!