• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ

 

የምክር ቤቱ 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤቱ አጀንዳዎች እና የምክር ቤቱ የ3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለጉባኤ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠልም የአስተዳደሩ አስፈጻሚ አካላትና የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ 6ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በተከበሩ የድራዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ቀርቦ በቋሚ ኮሚቴዎች ምክረ ሀሳብ እና በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተካሂዶበት ጸድቋል።

 

በጉባኤው የከሰአት በኋላ ውሎውም 4 የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ማለትም የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዥ እና የንብረት አስተዳደር አዋጅ ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈጻሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ፤ ከኃላፊነት የተነሱ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት መሪዎች፣ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤት አባላት የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች እና ዳኞች የሚያገኟቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 59/2010ን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ በቋሚ ኮሚቴዎች የውሳኔ ሀሳብ ከቀረበባቸው በኋላ በሙሉ ድምጽ እና በአብላጫ ድምጽ ጸድቀው ጉባኤው ተጠናቋል።

 

በአዲሱ ካሳ

ፎቶ፦ እንድሪያስ ደሱ     

 

#መረጃ | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️ 

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 

 

ድህረ-ገጽ [Website]

www.ddacouncil.gov.et 

 

ፌስቡክ [Facebook]

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d 

 

ዩቲዩብ [YouTube]

https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP 

 

ቲክ ቶክ [Tik Tok]

https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1 

 

ቴሌግራም [Telegram]

ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤ 

 

ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!