የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በዛሬው እለት የምክር ቤቱን የ3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 12ኛ መደበኛ ጉባኤ አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል ፡፡
የተከበሩ አፈ ጉባኤው በመግለጫቸውም የምክር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሰኔ 29 እስከ ሰኔ 30 /2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
በጉባኤውም የተለያዩ አጀንዳዎች ቀርበው በምክር ቤቱ አባላት ውይይት ተደርጎባቸው እንደሚጸድቁ ገልጸው የጉባኤው አጀንዳዎችም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 12ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማፅደቅ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ ፣ የአስተዳደሩ የአስፈጻሚና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2018ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ ፣ የምክር ቤቱ ተጠሪ ተቋማት የ2018 ዓ.ም እቅድ ሪፖርት እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ተጨማሪ በጀት ማጽደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የ2019 ረቂቅ በጀት ላይ ውይይት ተደርጎበት የሚያጸድቅ ይሆናል፡፡
በመሆኑም የተከበሩ የምክር ቤቱ አባላት በእለቱ በመገኘት በህዝብ የተጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ በምክር ቤቱ ስም ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በአዲሱ ካሳ
ፎቶ እንድሪስ ደሱ
#መረጃ | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!
ድህረ-ገጽ [Website]
www.ddacouncil.gov.et
ፌስቡክ [Facebook]
https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d
ዩቲዩብ [YouTube]
https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP
ቲክ ቶክ [Tik Tok]
https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1
ቴሌግራም [Telegram]
ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤
ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን
ይህን ዜና አጋራ