• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

 

20ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በመላው ኢትዮጵያ እንደሚከበር ይታወቃል።

 

በመሆኑም የበአሉን አከባበር አስመልክቶ የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

 

ክብርት አፈጉባኤዋ በመግለጫቸውም የዘንድሮው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል የብሄር ብሄረሰቦች አርማ የሆነው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ በተመረቀበት እንዲሁም የህዝቦች ጥያቄ የሆነው ሀገራዊ ምርጫ በሚደረግበት ወቅት የሚከበር በአል በመሆኑ ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።

 

የዘንድሮውን የብሄር ብሄረሠቦች በአል ስናከብር ህብረ ብሄራዊ አንድነታችንን በማጠናከር የዲሞክራሲ ግንባታችንን በማፋጠን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የለውጥ ጉዞ ለማሳካት ሁላችንም የምንረባረብበት መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃም በአሉን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ገልጸው ድሬዳዋ የሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች መገናኛ ድንቅ የፍቅር ከተማ እና ብሄር ብሄረሰቦች ተከባብረው በወንድማማችነት የሚኖሩባት እንደመሆኗ መጠን በአሉ ይህን እሴት በሚያሳይ መልኩ ለማክበር ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።

 

በመሆኑም በአሉ በአስተዳደር ደረጃ  ከዛሬው እለት ጀምሮ አስከ ህዳር 15 ድረስ በተለያዩ መርሀግብሮች ይከበራል ብለዋል።  በዚህም መሠረት በከተማና በገጠር በሚገኙ ሁሉም የመንግስት ተቋማት በፌዴራሊዝም እና ሀገረ መንግስት ግንባታ ዙሪያ የተዘጋጁ ሲምፖዚየሞች ፣ የማስ ስፖርት ፣ የባህል ፌስቲቫሎች  እንዲሁም ቶክሾዎች እና ሌሎች ዝግጅቶች እንደሚከበር ገልጸው የተከበረው መላው  የአስተዳደሩ ነዋሪ ለበአሉ ስኬት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

 

በአዲሱ ካሳ

ፎቶ ፦ እንድሪያስ ደሱ

 

#መረጃ  | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️ 

 

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ! 

 

ድህረ-ገጽ [Website]

www.ddacouncil.gov.et 

 

ፌስቡክ [Facebook]

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d 

 

ዩቲዩብ [YouTube]

https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil?si=TB3KelHlFoN6FhsP 

 

ቲክ ቶክ [Tik Tok]

https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq&_r=1 

 

ቴሌግራም [Telegram]

ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤ 

 

ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን!

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!