• info@ddacouncil.gov.et
  • 025-11-30654
News Photo

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም የም/ቤቱ የተሻሻለው የአሰራር እና የአባላት ስነምግባር ደንብ ቁጥር 39/2015 አንቀጽ 13 መሠረት የም/ቤቱ መደበኛ ጉባኤ በአመት ቢያንስ 2ጊዜ እንደሚካሄድ እንደሚገልጽ ጠቅሰው የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ከጥር 26 እስከ 27/2018 ድረስ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

በጉባኤውም ም/ቤቱ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን የሚሰጥ ይሆናል። በመሆኑም የጉባኤው አጀንዳዎች የም/ቤቱን የ3ኛ የስራ ዘመን 5ኛ አመት 3ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለጉባኤን ማጽደቅ ፣ የአስተዳደሩ የአስፈጻሚ አካላት እና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ግማሽ አመት አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ ፣ የተለያዩ አዋጆችን ማጽደቅ እንደሚሆኑ የተከበሩ አፈጉባኤው ጠቅሰው የም/ቤቱ አባላትም በጉባኤው ላይ በመገኘት ከህዝብ የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#መረጃ | ወቅታዊ እና ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት እነዚህን አማራጮች ይጠቀሙ ⬇️

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት መረጃዎችን ለማግኘት እነዚህን የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመከተል አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ!

ድህረ-ገጽ [Website]

www.ddacouncil.gov.et

ፌስቡክ [Facebook]

https://www.facebook.com/profile.php?id=100067680782694&mibextid=LQQJ4d

ዩቲዩብ [YouTube]

https://youtube.com/@diredawaadministrationcouncil...

ቲክ ቶክ [Tik Tok]

https://www.tiktok.com/@dire.administrati?_t=8rV9o39Vegq...

ቴሌግራም [Telegram]

ለተመራጭ የምክር ቤት አባላት ብቻ፤

ስለ አብሮነትዎ እናመሰግናለን

ይህን ዜና አጋራ

አስተያየት ይስጡ

ለህዝብ እና ለመንግስት ጥቅሞች ቅድሚያ የምንሰጥ ነን!